Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የእንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላለፉ

ዓርብ ነሐሴ 29, 2018 224

"ወዳጄ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ፤ በእርስዎ አስተዳደር ታሪካዊ ስኬት በመመዝገቡ በኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ ስም ከልብ የመነጨ ደስታዬንና እንኳን ደስ አለዎት መልእክቴን አቀርባለሁ" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/)

"እንደ ጠንካራ ሴት መሪ፣ አርቆ አሳቢ አመራር በዘመናዊዋ የጣሊያን ሪፐብሊክ ታሪክ ውስጥ ወደር የሌለው መረጋጋት አምጥቷል።"

የእርስዎ የማይናወጥ ቁርጠኝነት እና ጥንካሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ የብዙዎችን መንፈስ የሚያነሳሳ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ እና በጣሊያን መካከል ያለውን ጥልቅ እና ሁለንተናዊ አጋርነት ማጠናከሩን ቀጥሏል።

 

በመከባበር ላይ የተገነባውን የጋራ ቁርጠኝነታችንን በእጅጉ እናከብራለን፤ ለእርስዎ እና ለጣሊያን ሕዝብ ዘላቂ ሰላምና ብልጽግናን እመኛለሁ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: