የወላይታ ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል አከባበር አካል የሆነ የመስህብ ስፍራዎች ጉብኝት በወላይታ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ይገኛል።
ጉብኝቱ የጊፋታ መልካም እሴቶችን የማስተዋወቅ ዓላማ ያነገበ ሲሆን፣ የጊቤ 3 ሰው ሠራሽ ሐይቅ፣ ቡሻሻ ጋሯ (የነገሥታት መናገሻ)፣ የዳሞታ ተራራ እና አጆራ መንትያ ፏፏቴ ከመዳረሻዎች መካከል ይጠቀሳሉ።
በጉኝቱ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ ቲክቶከሮች እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እየተሳተፉ ነው።
የጉብኝት መርሐ ግብሩ ለተከታታይ 3 ቀናት እንደሚቀጥል የወላይታ ዞን ቱሪዝም መምሪያ አስታውቋል።
ጊፋታ በቅርቡ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ የዓለም ለቅርስነት መመዝገቡ ይታወሳል።
በተመስገን ተስፋዬ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: