Search

ኢቢሲ 'የጂ-ፓወር ቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ 2026'ን በብቸኝነት ለማስተላለፍ ስምምነት ተፈራረመ

ሓሙስ ነሐሴ 28, 2018 142

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) አራተኛውን ዙር የቲክቶክ ይዘት ፈጣሪዎች ውድድር ('የጂ-ፓወር ቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ 2026') በብቸኝነት ለማስተላለፍ ከቁሩንፉድ ዲጂታል ማርኬቲንግ ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራርሟል።

በዘንድሮው ውድድር የዕጩዎች መወዳደሪያ ዘርፎች ወደ 30 ያደጉ ሲሆን፤ አጠቃላይ የገንዘብ ሽልማቱ ከፍ ማለቱ እና ለአሸናፊውም ከአምናው የመኪና ሽልማት በተሻለ ዘመናዊ አፓርታማ እንደሚበረከት ተገልጿል።

ለሦስት ወራት በሚቆየው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት አልፈው አሸናፊዎቹ የሚለዩበት አጓጊ የማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት፣ ኅዳር ወር 2019 . በኢቲቪ መዝናኛ እና በዶትስትሪም የዲጂታል መድረኮች በቀጥታ ሥርጭት ለተመልካች ይቀርባል።

ይህ ውድድር ከመዝናኛነት መድረክነት ባለፈ የወጣቶችን የፈጠራ አቅም የሚያጎለብት፣ ኃላፊነት የሚሰማቸውን የይዘት ፈጣሪዎች በማበረታታት የሀገርን ገጽታ የሚገነባ እና የኢትዮጵያን የቱሪዝም መዳረሻዎች ለዓለም የሚያስተዋውቅ ሀገራዊ ተልዕኮን ያነገበ መሆኑን የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና የኢቢሲ ዶትስትሪም ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዶኒያስ ወልደአረጋይ አስገንዝበዋል።

የቁሩንፉድ አመራሮች የኢቢሲን ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ እና የዲጂታል ሽግግርን ጎብኝተዋል።

ተቋሙ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና ሰው ሠራሽ አስተውሎትን በመጠቀም ከአዲሱ ትውልድ ጋር በቅርበት ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጧል።

በኢንቲሃድ አብራር

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: