በኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መቐለ እና በመቐለ ዩኒቨርስቲ ትብብር 2ኛው ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ እና የኢንጂነሪንግ ጉባዔ ተካሂዷል።
“የላቀ ቴክኖሎጂ ለዘላቂ ልማት” በሚል ሃሳብ የተካሄደው ጉባዔ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ሃሳቦች የሚገኙበት እና በኢንጂነሪንግ እና ቴክኖሎጂ ዙርያ ያሉ ተግዳሮቶች እንዲሁም እድሎች የሚዳሰሱበት ነው ተብሏል።
የጉባዔው የትኩረት አጀንዳዎች ዘላቂ አርክቴክቸር የውሃ ማኔጅመንት በከተሞች እድገት፣ ታዳሽ ኃይል፣ የጨርቃ ጨርቅ ኢንጂነሪንግ፣ አግሮ ኢንዱስትሪ ቴክኖሎጂ እንዲሁም አዳዲስ ፈጠራዎች ላይ ያተኩራል ተብሏል።
ጉባዔው ከአምስት በኋላ መካሄዱ የተገለጸ ሲሆን፤ 39 የወቅቱ የቴክኖሎጂ የምርምር ፅሑፎች ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ተማራማሪዎች የወቅቱ የቴክኖሎጂ ውጤቶች እና ተግዳሮቶችን የሚያቀርቡ ሲሆን፤ በወይይቱ የሚያገኟቸውን ሃሳቦችም ለቀጣይ ምርምሮቻቸው ይጠቀሙባቸዋል ተብሏል።
ጉባዔው እስከ ነገ ቀጥሎ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
ሙሉጌታ ተስፋዬ