Search

ቻይና ከ6 ዓመት ጀምሮ ላሉ ልጆች የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ልታስተምር ነው

ረቡዕ ነሐሴ 14, 2017 173

ቤጂንግ 6 ዓመት ጀምሮ ላሉ ተማሪዎቿ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤ አይ) ትምህርትን ለመስጠት ማቀዷን አስታውቃለች፡፡

ከመጀመሪያ ደረጃ ምህርት ቤት ጀምሮ የሚሰጠው ትምህርቱ፤  ስለ ሰው ሰራሽ አስተውሎት አረዳድ፣ የመልዕክት ቦት አጠቃቀም እና የቴክኖሎጂው ሞያዊ ሥነ ምግባሮች ምንድናቸው?  በሚለው ላይ የሚያተኩር መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ይህም አሁን ላይ በቻይና የትምህርት ካሪኩለም  ውስጥ ባሉ የአይሲቲ፣ የሳይንስ እና ስታንድአሎን በተባሉ የትምህርት ዓይነቶች አማካኝነት የሚሰጥ መሆኑን የሀገሪቱ ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል፡፡

የቴክኖሎጂው ዘርፍ ፉክክር እና ጦርነት በቀጠለበት በዚህ ወቅት ቻይና አሸናፊ እንድትሆን በማሰብ  ውሳኔው መተላለፉ የተነገረ ሲሆን፤  የዲፕ ሲክ ሰርጎ በመግባት ተወዳዳሪ መሆን መቻል ሌላው ምክንያት እንደሆነም ተገልጿል፡፡

በቀዳሚነት በቤጂንግ የሚገኙ 184 የመጀመሪያ ደረጃ ምህርት ቤቶች ላይ ተግባራዊ የሚደረገው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ትምህርቱ፤  በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲስፋፋ ለማድረግ መምህራንን የማብቃት ስራ እንደሚሰራ ነው የተጠቆመው፡፡

ኢስቶኒያ፣ ካናዳ የእንግሊዝ የግል ምህርት ቤቶች እና ደቡብ ኮሪያ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን በአዳጊዎቻቸው ላይ ለማስረፅ ከመጀመሪያ ደረጃ ምህርት ቤት ጀምሮ እያስተማሩ የሚገኙ ሀገራት ናቸው፡፡

 በአፎሚያ ክበበው