የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ለኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ የሰላም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ አንድነት፣ ነጻነት እና የጋራ ምኞቶች ያበረከተችውን ታሪካዊ አስተዋጽኦ ያደነቁት ሊቀመንበሩ፣ ኮሚሽኑ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ያለውን አጋርነት በአዲሱ ዓመት አጠናክሮ ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቀዋል።
በአዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላምን፣ አንድነትን እና ብልጽግናን የተመኙት ሊቀመንበሩ፣ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የተባበረች፣ ሰላማዊ እና የበለጸገች አፍሪካን ዕውን ለማድረግ ከአጋር አካላት ጋር ተባብሮ ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) በተመሳሳይ፣ አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያ እና ለመላው የቀጣና ሀገራት አዲስ ተስፋን፣ ዘላቂ ሰላምን፣ የጋራ ብልጽግናን እንዲሁም የተሻለ አንድነትን ይዞ እንዲመጣ መልካም ምኞቱን ገልጿል።
ኢጋድ በመልዕክቱ፣ ለመላው ወንድም እና እኅቶቻችን እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ ብሏል። ዓመቱ የሰላም እና የብልጽግና እንዲሆንም ተመኝቷል።
በላሉ ኢታላ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: