የቡሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር፣ በቡሩንዲ ሕዝብ እና በአፍሪካ ኅብረት ስም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዳግም በጠቅላይ ሚኒስትርነት በመመረጣቸው የተሰማቸውን የላቀ ደስታ ገልጸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሊቀመንበሩ በመልዕክታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአዲሱ የሥራ ዘመናቸው ሙሉ ስኬት እንዲገጥማቸው ተመኝተዋል።
ኢትዮጵያ የያዘቻቸውን ስትራቴጂያዊ ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘላቂ ዕድገት፣ አንድነት እና ብልጽግናን እንደሚጎናጸፍ ያላቸውን የጸና ተስፋ ገልጸዋል።
አክለውም የአፍሪካ ኅብረት በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ አሕጉር ዘላቂ ሰላም፣ ቀጣናዊ መስተጋብር፣ የጠበቀ ትብብር እና የጋራ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እንዲሰፍን ከኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ ጋር በትብብር ለመሥራት ያለው ቁርጠኝነት የጸና መሆኑን ገልጸዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: