Search

የመደመር መንግሥት ምሥረታ አዲስ የሥልጣን ጅማሮ ብቻ አይደለም - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

ሰኞ መስከረም 25, 2019 137

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየማቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።  

በመልዕክታቸውም፣ “የመደመር ዕሳቤን በማፍለቅ፣ ሀገር ወዳድነትን በራዕይ በማጣመር እና ፈጠራን ከትጋት ጋር በማዋሐድ ለውጦችን የመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጥዎ እንኳን ደስ አለዎት” ብለዋል።

የመደመር መንግሥት ምሥረታ አዲስ የሥልጣን ጅማሮ ብቻ አይደለም፣ ከሕዝብ የተሰጠ አደራ እንደገና የተረከበበት ኃላፊነት ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን፤ በቀጣይም የተገኙ ስኬቶችን ማስቀጠል፣ ያሉ ችግሮችን ማረም፣ የሰላምን መሠረት ማጽናት፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ማፋጠን እና ለቀጣዩ ትውልድ ጠንካራ የሀገር መሠረት መጣል ዋና ዋና ተልዕኮዎቹ እንደሚሆኑ አመላክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚህ ትልቅ የኃላፊነት ቦታ ሀገራችንን በቅንነት፣ በጥበብ እና በጥልቅ የዓላማ ስሜት እንደሚያገለግሉ ሙሉ እምነት አለኝ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “በአገልግሎት ዘመንዎ የላቀ ስኬት እንዲኖርዎት እመኛለሁ” ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

#ትልቅ_ሀገር! #ትልቅ_ሕዝብ! #ታላቅ_ርዕይ!

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: