የሶማሊያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሐሙድ፣ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዳግም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየማቸው የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፕሬዝዳንቱ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲሱ የአገልግሎት ዘመናቸው የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የሶማሊያ እና ኢትዮጵያን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በጋራ ለመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል።
የሁለቱን ሀገራት ሕዝቦች እንዲሁም የአፍሪካ ቀንድ ቀጠናን ሰላም፣ መረጋጋት እና የጋራ ብልጽግና ለማረጋገጥ ከኢትዮጵያ ጋር በጥብቅ ትብብር እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል።
#ትልቅ_ሀገር! #ትልቅ_ሕዝብ! #ታላቅ_ርዕይ!
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: