የመደመር እሳቤ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለዜጎች ፈጣን እና ተደራሽ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሣሪያ አድርጎ በመቅረጽ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን አፋጥኗል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያስጀመሯቸው የ5 ሚሊዮን ኮደሮች መርሐ ግብር፣ የኢትዮጵያ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት ተቋማዊ ግንባታ እና የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ፖሊሲን ወደ ተግባር የመቀየር ቁልፍ ምዕራፎች ናቸው።
እነዚህ ሪፎርሞች ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሠራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ጤና ሻምፒዮን ሆነው እንዲሰየሙ መንገድ ከፍተዋል።
በጤና ተቋማት የኤሌክትሮኒክስ የመረጃ ሥርዓት መዘርጋቱ የታካሚዎችን የሕክምና ታሪክ በፍጥነት ለማግኘት እና የአገልግሎት እንግልትን ለመቀነስ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
የሰው ሠራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት ከጤና ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት በሽታዎችን አስቀድሞ ለመለየት እና የምርመራ ትክክለኛነትን ለማሳደግ የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎችን እያበለጸገ ይገኛል።
በ5 ሚሊዮን ኮደሮች መርሐ ግብር የሚሰለጥነው ወጣት ትውልድ ደግሞ የቴሌ-ሜዲስን መድረኮችን እና የሀገር ውስጥ ሶፍትዌሮችን በራስ አቅም ለማልማት ጠንካራ መሠረት ይጥላል።
የዲጂታል ጤና እና የመሠረተ ልማት መስፋፋት የሕዝብ ጤና ሥርዓትን በማዘመን ኢትዮጵያ የ5ኛውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ (CPHIA 2026) እንድታስተናግድ አቅም ፈጥሯል።
ከአንድ መቶ በላይ ሀገራት የተሳተፉበት ይህ መድረክ የዲጂታል ጤናን የወደፊት አቅጣጫ የቃኘ እና የኢትዮጵያን የጤና ዲፕሎማሲ ያጎላ ነው።
ኢትዮጵያ በሰው ሠራሽ አስተውሎት እና በዲጂታል ቴክኖሎጂ የጀመረችው ጉዞ የጤና አገልግሎትን ዘመናዊ፣ ፍትሐዊ እና ውጤታማ ለማድረግ ሰፊ ዕድል ከፍቷል።
በአድማሱ አራጋው
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: