Search

የኢትዮጵያን የማዕድን ዘርፍ በማጠናከር ሀገራችንን በውድ ማዕድናት ማጣሪያ ረገድ ቀጣናዊ ማዕከል እናደርጋለን፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ቅዳሜ መስከረም 30, 2019 108

በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና ተገንብቶ ሥራ የጀመረው ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ በአፍሪካ ደረጃ በግንባር ቀደምትነት የሚቀመጥና ከፍተኛ የአሠራር አቅም ያለው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ፋብሪካው በዓመት እስከ 80 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ምርት ኤክስፖርት የማድረግ አቅም ያለው ሲሆን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያለውን ሰፊ የማጓጓዣ አቅም በመጠቀም ከሀገር ውስጥ አልፎ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የሚወጣውን ወርቅ በማሰባሰብና በማጣራት ትልቅ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ይፈጥራል።

በወርቅ ዘርፍ ባለፈው ዓመት ከተላከው ከ5 እስከ 6 ቢሊዮን ዶላር ኤክስፖርት ውስጥ ይህ የማጣሪያ አቅም ቀደም ብሎ ቢኖር ኖሮ ገቢው እስከ 10 ቢሊዮን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትሩጠቁመዋል።

ቀደም ሲል 1 ኪሎ ወርቅ ሲላክ 70 በመቶው ብቻ ወርቅ ተብሎ ተይዞ፣ ቀሪው 30 በመቶው እንደ ቆሻሻ ይደፋ የነበረ ቢሆንም፣ ያ ተደፋ የሚባለው አካል እንደ ብር ያሉ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን ማዕድናት ያካተተ በመሆኑ በአዲሱ ማጣሪያ ከፍተኛ ጥቅም እንደሚገኝበት አብራርተዋል።

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በሳም ፕሬሺየስ ሜታልስ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት አጋርነት የተቋቋመውን ይህን ማጣሪያ ፋብሪካ የሚያንቀሳቅሱትና የሚያስተዳድሩት በዘርፉ የሰለጠኑ ሀገር በቀል ባለሙያዎች ናቸው።

 

በመሐመድ ፊጣሞ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: