Search

የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) የመቐለ 70 እንደርታ ተጫዋቾችን አበረታቱ

ማክሰኞ ኅዳር 15, 2019 28

 

የትግራይ ባለአደራ አስተዳደር መቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) በሐዋሳ ከተማ የሚገኙትን የመቐለ 70 እንደርታ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች በአካል በማግኘት፣ ለሚቀጥለው ጨዋታቸው በሙሉ አቅምና ቁርጠኝነት እንዲዘጋጁና ድል እንዲያስመዘግቡ የሞራል ድጋፍ በመስጠት አበረታትተዋል።

‎ከንቲባው ለተጫዋቾቹ በአካል መገኘታቸው ለክለብ ያላቸውን ድጋፍና በስፖርት ላይ ያላቸውን ትኩረት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።

‎የክለቡ ተጫዋቾች በሚቀጥለው ጨዋታ በሙሉ ልብ፣ በጋራ መንፈስና በከፍተኛ ቁርጠኝነት እንደሚጫወቱ ያላቸውን እምነትም ከንቲባው ገልጸዋል።

‎‎መቐለ 70 እንደርታ በሚቀጥለው ጨዋታ የተሻለ ብቃት በማሳየት ደጋፊዎቿንና የመቐለን ሕዝብ የሚያስደስት ውጤት እንደሚያስመዘግብ ይጠበቃል።

 

 

 

 

 

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: