የ5 ሚሊየን ወጣቶች የዲጅታል ሊትሬሲ ስልጠናን አላማ ያደረገ “የዲጂታል አማራ ኢኒሼቲቭ” ተጀመረ።
የዲጂል አማራ ኢኒሼቲቭ ማስጀመሪያ ስነ-ስርአት በባህርዳር ከተማ ተካሂዷል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በመርሃግብሩ እንደገለፁት፤ ዲጅታል ስልጠናው ወጣቶች የ21ኛው ዘመን ኢኮኖሚ ተሳታፊ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያግዛል ብለዋል።
በ 3 ምዕራፍ የሚተገበረው የዲጅታል አማራ ኢኒሼቲቭ ለ5ሚ ወጣቶች የዲጅታል ዕውቀት ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን መስጠት እና 120 ሺ ወጣቶችን በዲጅታል መስክ የሥራ ዕድል ማስያዝን አላማ ያደረገ መሆኑ ተናግረዋል።
ኢኒሼቲቩ ለ120 ሺ ወጣቶች የሥራ ዕድል የሚፈጥር ከሆኑም ባለፈ የዲጂታል አቅምን የሚያሳድግ መሆኑን አስረድተዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የአማራ ክልል ርዕሠ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ዋና ስራ አስኪያጅ ከሠተ ብርሃን አድማሱ (ዶ/ር) ፣ በአፍሪካ ልማት ማዕከል የአማራ ክልል የቅድመ ልጅነትና ስራዕድል ፈጠራ ኢንሼቲቭ አስተባባሪ አቶ አየልኝ ሙሉዓለም እንዲሁም የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣የዞን አስተዳዳሪዎችና ከንቲባዎችና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ሙያተኞች የተገኙበት ነው።
በራሔል ፍሬው
#EBC #ebcdotstream #coders