Search

ሻንጋይ የሮቦት ትራፊክ ፖሊስ ሥራ ላይ አዋለች

ቅዳሜ ነሐሴ 17, 2017 36

የቻይናዋ ከተማ ሻንጋይ የትራፊክ ፖሊስ ሥራ ላይ ማዋሏ ታውቋል።

ዣዎ ሁ (ትንሹ ነበር) የሚል ስም የተሰጠው ይህ ሮቦት የተጨናነቁ መንገዶች ላይ መኪኖችን በየተራ የሚያስተናግድ እንዲሁም ለመኪኖች ምልክት በመስጠት እግረኞችን እንደሚያሳልፍ ተገልጸል።

ይህን ለማድረግም የእጅ ምልክቶችን፣ ድምፅ እና የትራፊክ ፊሽካ እንደሚጠቀም ተነግሯል። ከዚህ ባለፈም የትራፊክ ትምህርቶችን ያስተላልፋልል።

የትራፊክ ፖሊሶች አይነት ዩኒፎርም ለብሶ በሻንጋይ ጎዳና የሙከራ ግዳጁን የተወጣው ዣን ሁ ልክ እንደ ትራፊክ ፖሊስ ሥራውን በትክክል ሲፈፅም መታየቱን ኒውዮርክ ፖስት ዘግቧል።

የሻንጋይ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ሮቦቱን ለመስራት አራት ዓመታትን ፈጅቶባቸዋል።

 

በዋሲሁን ተስፋዬ

 #EBC 3ebcdotstream #Traficpolice #robotics