Search

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተከፈተው የልማት ኤግዚቢሽንና የመደመር መንግሥት እመርታ

ማክሰኞ ጥቅምት 10, 2019 56

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በዱራሜ ተገኝተው ክልላዊ የግብርና ምርቶች ኤግዚቢሽን መርቀው ከፍተዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የበጋ ሥራዎች የንቅናቄ መድረክን አስመልክቶ የተዘጋጀው ይህ የግብርና ምርቶች ኤግዚቢሽን፣ አምራቹን አርሶ አደር እና ሸማቹን ማኅበረሰብ በቀጥታ የማገናኘት ታላቅ የገበያና የልማት እድል የፈጠረ ነው።

በኤግዚቢሽኑ ላይ ከዚህ ቀደም በክልሉ ያልተለመዱና አዳዲስ የሆኑ የግብርና ምርቶች ለእይታ እና ለገበያ የበቁ ሲሆን ይህም የሀገራችንን የግብርና ምርታማነትና የኢኖቬሽን አቅም አዲስ ከፍታ ላይ ማድረሱን በተግባር ያረጋገጠ እውነት ነው።

በክልሉ በመደመር መንግሥት ምስረታ ማግስት የተዘጋጀው ይህ የግብርና ምርቶች ኤግዚቢሽን አርሶ አደሩ በዘመናዊ ግብርና፣ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና እሴት በመጨመር ላይ ያለውን ግንዛቤ በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድግበት ታሪካዊ መድረክ መሆኑ ተጠቁሟል።

ይህ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተመዘገበ የግብርና እመርታ ኢትዮጵያ በፅኑ መሠረት ላይ የቆመች #ትልቅሀገር፣ በላቡና በሥራው ውጤታማነቱን ያስመሰከረ #ትልቅሕዝብ እና ለወደፊቱ የተዘረጋ #ታላቅርዕይ ያላት ሀገር መሆኗን በተግባር የሚያሳይ ነው።

 

በጠነከረ አገራዊ ፖሊሲና የተቀናጀ የሕዝብ ርብርብ የተገኘው ይህ ውጤት፣ በምግብ ራስን ለመቻልና የገበያ መረጋጋትን ለመፍጠር የሚደረገውን አገራዊ ጉዞ የሚያፋጥን ከመሆኑም በላይ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አርሶ አደሮች ወደ ዘመናዊና መዋቅራዊ የግብርና ቢዝነስ የመሸጋገራቸው ትልቅ ማረጋገጫ ሆኗል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: