Search

ፒኤስጂ ከ ባርሴሎና - ታላቅ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍልሚያ በፓሪስ

ማክሰኞ ጥቅምት 10, 2019 32

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሦስተኛ ሳምንት የሊግ መርኃ ግብር ዛሬ ምሽት 4፡00 ሰዓት ላይ በፓርክ ደ ፕሪንስ ስታዲየም፣ በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ የተቀመጡት ፒኤስጂ እና ባርሴሎና ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች 10 ግቦችን በማስቆጠር በ6 ነጥብ እና በ7 የግብ ክፍያ የደረጃ ሰንጠረዡን እየመራ የሚገኘው የፈረንሳዩ ፒኤስጂ፣ ባለፈው ሳምንት ማንቸስተር ሲቲን በሜዳው 4 ለ 2 በማሸነፍ አስደናቂ የበላይነት አሳይቷል።

በሻምፒዮንስ ሊጉ ላለፉት 12 ጨዋታዎች ሽንፈት ያልገጠመው የፓሪሱ ክለብ፣ በሁሉም ውድድሮች ተከታታይ ስድስት ድሎችን በማስመዝገብ በከፍተኛ የአሸናፊነት ስነ-ልቦና ላይ ሆኖ ለዛሬው ጨዋታ ዝግጁ ሆኗል።

በአንጻሩ በአሠልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ የሚመራው ባርሴሎና በውድድር ዓመቱ ያደረጋቸውን 11 ጨዋታዎች በሙሉ በድል ያጠናቀቀ ሲሆን፣ 48 ግቦችን (በአማካይ 4.4 ግብ በጨዋታ) በማስቆጠር በአውሮፓ እጅግ አስፈሪ የማጥቃት ብቃት እያሳየ ይገኛል።

በውድድሩ ፌይኖርድን እና ጋላታሳራይን በሰፊ የግብ ልዩነት በማሸነፍ 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው የካታላኑ ክለብ፣ በተከታታይ አራት የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች አራትና ከዚያ በላይ ግቦችን በማስቆጠር ታሪክ ቢሰራም፣ በፍሊክ የአጨዋወት ዘይቤ ስር በተከላካይ ክፍሉ ላይ የሚስተዋለው ክፍተት ለዛሬው የፓሪስ ፈተና ትልቅ ጥንቃቄ የሚሻ ጉዳይ ሆኖ ይነሳል።

የባርሴሎናው የ19 ዓመት ኮከብ ላሚን ያማል በዘንድሮው ሻምፒዮንስ ሊግ በሁለት ጨዋታዎች ብቻ አምስት የግብ ተሳትፎዎችን በማድረግ (1 ግብ በማስቆጠር  እና 4 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል) ድንቅ ብቃት ላይ ይገኛል።

ሁለቱ ቡድኖች በታሪካቸው ባደረጓቸው 16 የእርስ በእርስ ግንኙነቶች እኩል 6 ድሎችን ያስመዘገቡ ሲሆን፣ ፒኤስጂ የመጨረሻዎቹን ሁለት ጨዋታዎች በድል ተወጥቷል።

በባርሴሎና በኩል ኤሪክ ጋርሲያ እና ጁለስ ኩንዴ እንዲሁም በፒኤስጂ በኩል ደግሞ ኑኖ ሜንዴዝ ጉዳት ከዛሬው ጨዋታ ውጪ ያደረጋቸው ተጫዋቾች ናቸው፡፡

በሌላ የዛሬ ምሽት 4፡00 ሰዓት ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ በኢቲሃድ ስታዲየም የግሪኩን ክለብ ኤኢኬ አቴንስን ያስተናግዳል።

ባለፈው ሳምንት በፒኤስጂ ሽንፈት የደረሰበት ማንቸስተር ሲቲ የመስመር አጥቂውን አንትዋን ሴሜንዮ በጉልበት ጉዳት የማያሰልፍ ሲሆን፣ ኤርሊንግ ሃላንድም በጨዋታው የመሰለፉ ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኗል።

በውድድሩ ከእንግሊዝ ክለቦች ጋር ባደረጋቸው ያለፉት ስምንት ጨዋታዎች ሰባቱን የተሸነፈውና በሻምፒየንስ ሊጉ ታሪክ ከሜዳው ውጪ የማሸነፍ ታሪክ የሌለው ኤኢኬ አቴንስ፣ ከግሪክ ክለቦች ጋር ባደረጋቸው ጨዋታዎች ሽንፈት ቀምሶ በማያውቀው ማንቸስተር ሲቲ ከባድ ፈተና እንደሚገጥመው ይጠበቃል።

በሌሎች የዛሬ የሻምፒዮንስ ሊግ መርኃ ግብሮች ምሽት 1፡45 ላይ ፌነርባቼ ከ ስላቪያ ፕራግ እንዲሁም ሳባህ ኤፍኬ ከ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ይጫወታሉ።

ምሽት 4፡00 ሰዓት ላይ ደግሞ ሊቨርፑል ከ ቪያሪያል፣ ፖርቶ ከ ፒኤስቪ አይንድሆቨን፣ ስቱትጋርት ከ አትሌቲኮ ማድሪድ፣ ናፖሊ ከ ቦዶ/ግሊምት እንዲሁም ሮማ ከ ስሎቫን ብራቲስላቫ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ።

በዘረንቶስ ሰለሞን

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: