በአማራ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች የሀገር መከላከያ ሠራዊት ለሀገር ሉዓላዊነት እየከፈለ ያለውን መስዋዕትነት የሚደግፍ፣ እንዲሁም የውስጥ እና የውጭ የታሪካዊ ጠላቶቻችንን እኩይ ተግባር የሚቃወም ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ ከጠዋቱ ጀምሮ ተካሂዷል።
ይህ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በደሴ፣ በደብረ ሲና፣ በጣርማ በር፣ በዱርቤቴ፣ በአዴት፣ በመርሃቤቴ ፌጥራ ከተሞችና በሌሎች ከተሞች ህዝቡ በነቂስ በመውጣት የተካሄደ ነው።
በሰልፉ ላይ የተሳተፉ በርካታ የክልሉ ነዋሪዎች የመከላከያ ሠራዊቱን ፅናት፣ ጀግንነትና ድል አድራጊነት የሚያወሱ እንዲሁም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስከብሩ መለክቶችን አስተጋብተዋል።
ከተንጸባረቁት መልዕክቶች መካከል የጀግናውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት እንደግፋለን፣ በፋኖ ስም የሚንቀሳቀሰውን የፅንፈኛውን ሃገር ሻጭነትና ባንዳነት እናወግዛለን፣ የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት በልጆቿ መስዋዕትነት እውን ይሆናል፣ እንዲሁም ከታላቁ የሕዳሴ ግድባችን ወደ ቀይ ባሕር ወደባችን የምናደርገውን ታሪካዊ ሽግግር እውን እናደርጋለን የሚሉት ይገኙበታል።
ነዋሪዎቹ የሕዝብ ልጅ ከኾነው ሠራዊት ጎን በጽናት እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።
ይህ በአማራ ክልል ከተሞች የታየው ሕዝባዊ መነሳሳት ኢትዮጵያ በፅኑ መሠረት ላይ የቆመች #ትልቅሀገር፣ በወንድማማችነት የተሳሰረ #ትልቅሕዝብ እና ወደ ወደብና ቀጠናዊ ከፍታ የሚያሸጋግር #ታላቅርዕይ ያላት ሀገር መሆኗን ያረጋገጠ ነው።
በተስፋሁን ደስታ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: