ኢትዮጵያ በታሪኳ አኩሪ፣ በነፃነቷ የማይደራደሩ ጀግኖች ልጆች ባለቤት የሆነች ታላቅ ሀገር ናት። ዛሬ ላይ ተቋማዊ ማሻሻያዎችን በማካሄድ በዘመናዊ ትጥቅ፣ በላቀ ቴክኖሎጂ እና በሰለጠነ የሰው ኃይል የተገነባው የመከላከያ ሠራዊታችን፣ የሀገራችንን ሉዓላዊነትና ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ በማስጠበቅ ረገድ የማይተካ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
ይህ ታላቅ የመከላከያ ተቋም ጠላትን የሚያሸንፍ ብቻ ሳይሆን፣ ገና ሳይዋጋ ውጊያን የመግታት እና በሀገራችን ላይ ክፉ ያሰቡትን ሁሉ የሚያስከዳ ከፍተኛ ዝግጁነትና ብቃት ያለው ነው።
ዘመናዊ እና የተጠናከረ የፀጥታ ተቋም መገንባታችን ለሀገራችን የከፍታና የልማት ጉዞ፣ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት አስተማማኝ ዋስትና ሆኖ ያገለግላል። ጠንካራ ተቋም፤ አስተማማኝ ሉዓላዊነት!
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: