Search

ለኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ እርሾ የሆኑ ሀገራዊ እሴቶች ወደ ገበያው መምጣት አለባቸው - ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

እሑድ ነሐሴ 18, 2017 54

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (/) “ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ፍለጋበሚል ርዕስ ተጽፎ ለአንባብያን በደረሰው መፅሐፍ ዙሪያ በተለያዩ የሥራ መስኮች የሚገኙ ባለሙያዎች እና ከፍተኛ ሥራ ኃላፊዎች ውይይት አድርገውበታል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በዚሁ ወቅት፥ ለዴሞክራሲርዓት ግንባታ እርሾ የሆኑ ሀገራዊ እሴቶች ወደ ገበያው መምጣት አለባቸው ሲሉ ገልፀዋል

የጋዜጠኝነት እናነ-ተግባቦት ባለሙያ እና ተመራማሪ አቶ ከማል ሀሺ፥ በተለይ ከለውጡ በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) አርአያነትን በመከተል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ያካበቱትን ልምድ እና እውቀት በመፅሐፍ መልክ ለሕዝቡ ማካፈላቸው የሚያስመሰግን ልምምድ መሆኑን ተናግረዋል።

"ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ፍለጋ" በሚል ርዕስ በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (/) በቅርቡ ያሳተሙት መፅሐፍ ከፍተኛ የምርምር ሥራዎች የታዩበት እና ለምንፈልገው ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ታላቅ አበርክቶ ያለው ስለመሆኑም አቶ ከማል አብራርተዋል።

የፍልስፍና ምሁር እና ተመራማሪው አቶ ዘሪሁን ተሾመ በበኩላቸው፥ ዴሞክራሲን ከሌሎች ሀገራት በመቅዳት ኢትዮጵያ ውስጥ ለመተግበር የተደረጉ ጥረቶች ውጤት እንዳላመጡ አንስተዋል። 

በዚህ ረገድ "ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ፍለጋ" በሚል ርዕስ የተፃፈው የተስፋዬ በልጅጌ (/) መፅሐፍ ለሀገር በቀል እውቀት ትኩረት በመስጠት ኢትዮጵያን የሚመስል ዴሞክራሲ ለመገንባት የሚያስችል ጥረት እንደሆነ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረትም ይህንኑ ሀሳብ በማጠናከር፥ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ የሽምግልና፣ የእርቅ፣ የሕግ እና ሌሎች ለዴሞክራሲርዓት ግንባታ የሚጠቅሙ እሴቶች እንዲታወቁ የማድረጉ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

#ኢቢሲዶትስትሪም #ተስፋዬበልጅጌ(/) #ኢትዮጵያዊዴሞክራሲፍለጋ