Search

የአዲስ አበባ ለውጥ በህልም እንኳ የማይታሰቡ ስኬቶች እውን መሆን እንደሚችሉ ማሳያ ነው፡- ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀሥላሴ

ሰኞ መጋቢት 07, 2018 54

በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች፣ በኢትዮጵያ እውን ይሆናሉ ተብለው የማይታሰቡ ስኬቶች መገኘታቸውን የሚያረጋግጡ መሆናቸውን ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀሥላሴ ገለጹ።
ፕሬዚዳንቱ ይህንን ያሉት ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል በተዘጋጀ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው።
ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው "ይህች ሀገር እንዲህ ትለወጣለች የሚል እይታ በህልማችንም የምናየው አልነበረም" ብለዋል።
ሆኖም በትጋት መሥራትና ትክክለኛውን አቅጣጫ መከተል ከተቻለ፣ ከማንም ሀገር የማይተናነስ ዋና ከተማ መገንባት እንደሚቻል በተግባር እየታየ መሆኑን ገልጸዋል።
እያንዳንዱ መሪ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለውጥ አመጣለሁ ብሎ በቁርጠኝነት ከተነሳ የማይፈጸም ነገር እንደሌለ የጠቀሱት ፕሬዚዳንቱ፤ ለዚህ ስኬት የሕዝብ ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል።
እውነተኛ ከተሜነት የሐሳብ ለውጥ ውጤት መሆኑን ያስገነዘቡት ፕሬዚዳንት ታየ፣ ልማቱ የሚፈጥረው ብሩህነት እንደ ንቃት ብርሃን (Enlightenment) የሚታይና ለአዳዲስ የፈጠራ ሐሳቦች መንገድ የሚከፍት መሆኑን አስረድተዋል።
እነዚህ የለውጥ ሥራዎች የጠራ የአመራር አቅጣጫና የቁርጠኝነት ውጤቶች መሆናቸውንም አብራርተዋል።
በላሉ ኢታላ