Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነዳጅን በኃላፊነትና በቁጠባ እንድንጠቀም አሳሰቡ

ሰኞ መጋቢት 07, 2018 64

በመካከላኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ቀውስ የተነሣ ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገሮች እንደልብ ለማግኘት ተቸግረዋል።
በመሆኑም ችግሩ ተፈትቶ ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስክንመለስ ድረስ ነዳጅን በቁጠባና ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም ይኖርብናል።
በመሆኑም የነዳጅ አከፋፋዮች፣ማደያዎች እና ተጠቃሚዎች ነዳጅን በቁጠባ፣ ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት ሁላችንም በሃላፊነት ስሜት እንድንጠቀም ለማሳሰብ እወዳለው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።