Search

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን የማስተናገድ ዕድል ሊሰጣት ይገባል - የጋና ፕሬዚዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ

ቅዳሜ ጥቅምት 14, 2019 37

በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ባለው 12ኛው የጣና ከፍተኛ የደህንነት ፎረም ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የጋና ፕሬዝደንት እና የጣና ፎረም ቦርድ ሊቀመንበር ጆን ድራማኒ ማሃማ የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን ጎብኝተዋል።

ፕሬዝደንቱ በጉብኝታቸው ወቅት ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ያቀረበችው ጥያቄ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።

ፕሬዝደንት ጆን ድራማኒ ማሃማ የባህር ዳር ስታዲየም አስደናቂ መሠረተ ልማት የተሟላለት መሆኑን ጠቅሰው፣ ስታዲየሙ 52,000 ተመልካቾችን የመያዝ አቅም እንዳለውና ከአፍሪካ እግር ኳስ ማህበር (ካፍ) ቀደም ሲል ደረጃውን የጠበቀ ሰርተፊኬት ማግኘቱን አስታውሰዋል።

"ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሩን ካስተናገደች በጣም ረጅም ጊዜ ሆኗታል፤ስለዚህ ይህንን ዕድል ማግኘቷ ተገቢ ይመስለኛል" ያሉት ፕሬዝደንቱ፣ ኢትዮጵያ ስኬታማ ውድድር ለማስተናገድ የሚያስችሉ ዘመናዊ የስፖርት ልማት አውታሮችና ፋሲሊቲዎች እንዳሏት አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያም ውድድሩን በላቀ ደረጃ ለማስተናገድ ሙሉ ዝግጅት ላይ እንደምትገኝ እምነታቸውን ገልጸዋል።

በመሀመድ ፊጣሞ

 

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: