Search

የሉዓላዊነት ዋልታ፣ የሕዝብ ደኅንነት ጋሻና የብሔራዊ ጥቅም ዘብ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት

ቅዳሜ ጥቅምት 14, 2019 36

የሀገር ታላቅነት ከሰነቀችው ርዕይ ባሻገር ርዕዩን በተግባር በሚያሳኩ አስተማማኝ ተቋማት የሚለካ መሆኑን በማስገንዘብ፣ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀዳሚው ነው።

ኢትዮጵያ የምትመኘውን የልማት፣ የሰላምና የብልፅግና ግብ ለማሳካት አስተማማኝ ተቋማትን በጽኑ መሠረት ላይ በመገንባት ላይ ትገኛለች።

በተለይም ሰላምን የሚያስጠብቁ፣ ደኅንነትን የሚያረጋግጡ፣ የሕግ የበላይነትን የሚያሰፍኑና የዜጎችን መብት የሚያስከብሩ ተቋማት የሀገራዊ ልማትና የሀገር ህልውና ዋነኛ መሠረቶች ናቸው።

ሰላም ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴዎችን ለማፋጠን መሠረታዊ ሁኔታ በመሆኑ፣ የተረጋጋ አካባቢያዊና ሀገራዊ ምኅዳር ለመፍጠር የመከላከያ ሠራዊት፣ የፖሊስ፣ የመረጃና ደኅንነት ተቋማት እንዲሁም የፍትሕ አካላት ሕጋዊ ኃላፊነታቸውን በዘመናዊ ዕውቀትና በሙያዊ ብቃት በላቀ ደረጃ እየተወጡ ይገኛሉ።

በሰራዊት ቀን የሚታየውም የሀገራችን የመከላከል አቅም፣ ኢትዮጵያ በሰነቀችው ታላቅ ርዕይ መሠረት የሕዝቧን ታላቅነት የሚመጥኑ የፀጥታና ደኅንነት ተቋማትን እየገነባች መሆኗን ማረጋገጫ ነው።

የኢትዮጵያና የሕዝቦቿ ታላቅነትም ሰላምን በማስጠበቅ፣ የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥና ተቋማቷን በዘመናዊ አደረጃጀት በማጠናከር በተግባር እያረጋገጠችው ያለች እውነታ ነው።

 

ይህ ታሪካዊና ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊታችን የደረሰበት አስተማማኝ የከፍታ ደረጃ፤ ኢትዮጵያ በጽኑ መሠረት ላይ የቆመች #ትልቅሀገር፣ በጀግንነትና በሥነ-ምግባር የታነጸ #ትልቅሕዝብ እና ወደ ላቀ ብልፅግናና ሰላም የሚያሸጋግር #ታላቅርዕይ ያላት ሀገር መሆኗን በግልጽ ያሳያል።

 

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: