ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 12ኛውን የጣና ፎረም ከተከታተሉ በኋላ፣ ከአፍሪካ መሪዎችና ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በመሆን በባሕር ዳር ስታዲየም ጉብኝት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ጉብኝት በሀገራችን በስፖርት መሠረተ ልማት ረገድ እየታየ ያለውን ተጨባጭ መሻሻል በግንባር ቀደምነት ያሳየ ነው። አክለውም ባሕር ዳር ለስፖርት፣ ለቱሪዝም እና ለአህጉራዊ እንዲሁም ቀጠናዊ ትብብር ማዕከል ከመሆን አንጻር ያላትን ታላቅ አቅምና ዝግጁነት ለአፍሪካውያን መሪዎችና ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተግባር ለመመስከር ጥልቅ ዕድል የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ የከፍተኛ አፍሪካውያን መሪዎች የስታዲየም ጉብኝት፤ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ሁነቶችን በብቃት የማስተናገድ አቅም ያላት #ትልቅሀገር፣ ለእስፖርትና ለቱሪዝም እድገት ትልቅ ትኩረት የሚሰጥ #ትልቅሕዝብ እንዲሁም ቀጠናዊ ትስስርንና አህጉራዊ ከፍታን የሚያረጋግጥ #ታላቅርዕይ ያላት ሀገር መሆኗን ማረጋገጫ ነው።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: