በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ሳምንት ወደ ቪላ ፓርክ አቅንቶ አስቶንቪላን የገጠመው ማንቸስተር ሲቲ 2 ለ 1 ተሸንፎ፣ በውድድር ዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ነጥብ ጥሏል።
በመጀመሪያው አጋማሽ 6ኛው ደቂቃ ኒኮላስ ጃክሰን ያስቆጠራት ግብ ቪላን መሪ አድርጋ የነበረ ቢሆንም፣ ኤርሊንግ ሃላንድ 52ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ግብ ጨዋታውን 1 ለ 1 አቻ አድርጋለች።
ከስምንት ደቂቃዎች በኋላ ግን ኒኮላስ ጃክሰን አስቶንቪላን 2 ለ 1 አሸነፊ ያደረገች ግብ አስቆጥሮ፣ ቡድኑ ሦስተኛውን ድል በማስመዝገብ ነጥቡን 11 እንዲያደርስ አስችሏል።
በውድድር ዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሸነፈው ማንቸስተር ሲቲ 21 ነጥብ እንደያዘ ቢቀጥልም የደረጃ ሰንጠረዡን መሪነት አልተነጠቀም።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: