ኢትዮጵያ 12 የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ (Su-35 4++ Generation) የጦር ጄቶችን ከሩሲያ መረከቧን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት ዛሬ ሌላ አዲስ ምዕራፍ ደርሷል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በመከላከያ ኃይሏ እያደረገች ያለችው ዝግጁነት ጥቃትን ቀድሞ ማስቀረት የሚያስችላትን አቅም እያላበሳት መሆኑንም አብራርተዋል።
ከዚህ ቀደም ከሩሲያ መንግሥት ጋር በተደረሰው ስምምነት መሠረት፣ የመጀመሪያዎቹ 12 የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄቶች የተረከቡ ሲሆን፤ በተጨማሪም ኢትዮጵያ አራት የኤስ-400 (S-400) የአየር መከላከያ ሥርዓት ባትሪዎችን እንደምትረከብ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ "ወዳጄ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከስምምነታችን አንድ ዓመት አስቀድሞ እነዚህን የጦር አውሮፕላኖች እንድንረከብ ስላሳዩት ትጋት ላመሰግናቸው እወዳለሁ" ብለዋል።
እነዚህን ዘመናዊ የጦር ጄቶች በመታጠቅም ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚ ለመሆን መበቃቷን ገልጸዋል።
ይህ ታሪካዊ ስኬት የሀገራችንን ሉዓላዊነት ይበልጥ የሚያጠናክር ሲሆን፣ ወደፊትም የጋራ ደህንነታችንን እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጉዞ በልበ ሙሉነት ለመቀጠል ትልቅ አቅም እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: