Search

ከወደ እስያ 586 ሺ ዜጎች ከአደጋ ቀጠና በአስቸኳይ እንዲወጡ ታዘዙ

እሑድ ነሐሴ 18, 2017 44

በእስያዋ ሀገር ቬትናም “ታይ ፎን ካጂኪ” በተባለ ከውቂያኖስ የሚነሳ ወጀብ ልትመታ መሆኑን የሀገሪቱ የአየር ትንበያ ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል።
 
በዚህም የተነሳ የሀገሪቷ መንግስት 586 ሺ የሀገሪቱ ዜጎች ከአደጋ ቀጠና በአስቸኳይ እንዲወጡ ማዘዙን ቢቢሲ ዘግቧል።
 
 
 
ከሰሜን ፓስፊክ ውቂያኖስ የተነሳው ታይ ፎን ካጂኪ በሰዓት 166 ኪ.ሜ እየተጓዘ ወደ ቬትናም ባህር ዳርቻ እየገሰገሰ እንደሚገኝ የዘርፉ ሳይንቲስቶች ገልጸዋል።
 
በአየር ንብረት ለውጥ የተነሳ የዓለም ሙቀት ጨምሯል፤ በዚህም ግግር በረዶዎች እየቀለጡ በየጊዜው የባህር ወለል ከፍታ እየጨመረ ይገኛል።
 
ይህ ደግሞ በውቂያኖሶች ዳርቻ ለሚገኙ ሀገራት ከፍተኛ ስጋት እየፈጠረ መሆኑ ተጠቁሟል።
 
 
በዳንኤል ብዙዓየሁ