Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሞተራቸው ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የተቀረላቸው የመጀመሪያዎቹ 26 አውቶብሶች ሥራ በጀመሩበት ወቅት ያስተላለፉት መልዕክት ዋና ዋና ነጥቦች

ዓርብ ጥቅምት 20, 2019 94

 

👉 በጎዴ ተጀምሮ የነበረው የመጀመሪያው ምዕራፍ የተፈጥሮ ጋዝ ማውጣት ሥራ ፍሬ አፍርቶ ለተጠቃሚ ማድረስ ተጀምሯል። 👉 ጋዝ በፈሳሽ ነዳጅ ፎርም ስላልሆነ ከጉድጓድ አውጥቶ ለተጠቃሚ ማድረስ ተጨማሪና ልዩ የትራንስፖርት ዝግጅትን ይጠይቃል። 👉 የነዳጅ ማደያ ለጋዝ አገልግሎት ስለማይሆን በአዳማ እና በሌሎች አካባቢዎች ለጋዝ የሚሆኑ ልዩ ማደያዎች ተገንብተዋል። 👉 ጋዙን ከምርት ቦታው (ከጎዴ) ወደ ማደያዎች ለማጓጓዝ የሚያስችሉ ልዩ የጋዝ ታንከሮች ተዘጋጅተዋል። 👉 ቀደም ሲል በአዲስ አበባ አንበሳ ባስ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ የናፍጣ ባሶች ሞተራቸው ወደ ጋዝ እንዲቀየር ተደርጓል። 👉 ባለፉት ጥቂት ወራት 26 አውቶብሶች ሙሉ በሙሉ ሞተራቸው ተቀይሮ ለጋዝ አገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል። 👉 የባሶችን ሞተር የመቀየር ሥራ ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ፣ የተፋጠነ ለውጥ ለማምጣት 400 አዳዲስ የጋዝ ባሶች ታዝዘው በ3 ወራት ውስጥ ይገባሉ። 👉አዳዲሶቹ 400 የጋዝ ባሶች ሲገቡ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ያለውን የአንበሳ ባስ አገልግሎት 34% ይሸፍናሉ። 👉 በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ የሕዝብ ትራንስፖርት ባሶች ሙሉ በሙሉ ወደ ጋዝ ይቀየራሉ። 👉 የጋዝ አጠቃቀም የትራንስፖርት ወጪን አሁን ካለው አሰራር በትንሹ 50% ይቀንሳል። 👉 የትራንስፖርት፣ የቤት እና የምግብ ወጪዎችን በመቀነስ የዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች የኑሮ መከራ ማቃለል ዋናው ግብ ነው። 👉 የመንግሥት ስኬት መለኪያው ማቀድና መናገር ብቻ ሳይሆን ፈተናዎችን አልፎ ሥራዎችን አጠናቆ ለሕዝብ ጥቅም ማዋል ነው። 👉 ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥም ሆነ በአፍሪካ ደረጃ የተናገረችውን የምትፈጽምና የምታሳካ ሀገር በመሆን ስሟ እየጎላ መጥቷል። 👉 የትራንስፖርት እና የምርት ግብአቶችን በሀገር ውስጥ ሀብት በመተካት ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት መቀነስ ያስፈልጋል። 👉 የሞጆ እና የደብረብርሃን የሴራሚክስ ፋብሪካዎች ወደ ጋዝ የተቀየሩ ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ የሴራሚክስ ፍላጎትን ከ100% በላይ ይሸፍናሉ። 👉 ፋብሪካዎች በጋዝ ማምረታቸው እና ምርቶችን በጋዝ ትራኮች ማጓጓዝ መጀመሩ የቤት ግንባታ ወጪ እንዲቀንስ ያደርጋል። 👉 የጋዝ አጠቃቀም ከውጭ የሚገባውን ነዳጅ በመተካት የውጭ ምንዛሬ ፍላጎትን ይቀንሳል፤ የዋጋ ንረትንም ለመቆጣጠር ይረዳል። 👉 ከፋብሪካ ወደ ግንባታ ቦታዎች ቁሳቁስ የሚያጓጉዙ 100 የጋዝ ትራኮች ታዝዘው በ2-3 ወራት ውስጥ ይገባሉ። 👉 በምዕራፍ ሁለት የሚመረተው ጋዝ ለማዳበሪያ ምርት እና ኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት አገልግሎት ላይ ይውላል። 👉 ሀገር በአንድ ጅምር ስለማትገነባ ዜጎች በተስፋ፣ በትጋት እና በህብረት (“በመደመር”) ለሀገር ዕድገት እንዲሰሩ ጥሪ ቀርቧል።

 

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: