Search

የትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር በመቐለ ከተማ በቀጣይ የሚከናወኑ ሥራዎችን ለማስፈጸም የሚያስችሉ አቅጣጫዎች አስቀመጠ

እሑድ ጥቅምት 22, 2019 52

የመቐለ ከተማ ባለአደራ አስተዳደር ባካሄደው ስብሰባ በከተማዋ በቀጣይ የሚከናወኑ ዓበይት ተግባራትን በተቀናጀ መልኩ ለማስፈጸም የሚያስችሉ ውሳኔዎችን እና አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

የትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) መሪነት በተካሄደው በዚህ የምክክር መድረክ፣ በከተማዋ የደረሱ ውድመቶችን መልሶ የመገንባት፣ የተቋማትን የአገልግሎት አቅም የማጠናከርና አስተዳደራዊ አሠራሮችን ቀልጣፋ የማድረግ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በተጨማሪም እስካሁን የተከናወኑ ሥራዎች የተገመገሙ ሲሆን፣ የነዋሪዎችን የአገልግሎት ጥያቄዎች ሳይዘገይ ለመመለስ እና አፋጣኝ ምላሽ የሚሹ አጀንዳዎችን በመለየት የተቀናጀ የሥራ አቅጣጫ ተቀምጧል።

 

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: