በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት በኢቲሃድ ስታዲየም ብራይተንን ያስተናገደው ማንቸስተር ሲቲ 1 ለ 0 ተሸንፏል።
ከቀናት በፊት ከካራባዎ ዋንጫ ያሰናበታቸው ሲቲ ላይ የብራይተንን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ 12ኛው ደቂቃ ላይ ያሲን አያሪ ከመረብ አሳርፏል።
ብራይተን በዘጠኙ ሳምንታት መርኃ ግብሮች ከሁሉም የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በመላቅ በተጋጣሚዎቹ መረብ ላይ 24 ግቦችን አስቆጥሯል።
በሊጉ ለተከታታይ ሁለተኛ ጊዜ የተሸነፈው ማንቸስተር ሲቲ 21 ነጥብ እንደያዘ ቀጥሎ የሊጉን መሪነት ባይነጠቅም፣ ነገ አርሰናል ሊቨርፑልን በሚገጥምበት ጨዋታ የሚመዘገብ ውጤት ደረጃውን ሊያሳጣው ይችላል።
ዛሬ ስድስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ብራይተን ደግሞ በ19 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: