ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ግመታን ወቅታዊ ማድረግ ( GDP REBASING ) ስራ በስኬት መጠናቀቁን የሚያበስር ሀገራዊ መድረክ በብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት በአዲስ አበባ ተዘጋጅቷል። በመርሀ ግብሩ ፖሊሲን ከማቀናጀት አንጻር፡ የተሻሻለው የጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት መረጃ ለፊስካል (በጀት እና ግብር)፣ ለሁለገብ የገንዘብ ፖሊሲ እና ለልማት እቅድ ዝግጅት እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል ይዳሰሳል። ✅ የመረጃ ማመንጨት ሥርዓታችን ምን ያክል እንደ ዘመነ፦ የህዝብ ቆጠራዎችን፣ የቤተሰብ ጥናቶችን፣ የአስተዳደር መረጃዎችን እና ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም መረጃዎችን በየጊዜው ማዘመን ላይ ያለንበት ደረጃ ይብራራል። ✅ መረጃን ተደራሽ ከማድረግ አኳያ፡ መረጃዎችን በወቅቱ ይፋ ከማድረግ አንጻር የደረስንበትን አጠቃላይ ቁመና ዙርያ ገለፃ ይደረጋል።
ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ግመታን ወቅታዊ ማድረግ ሥራ መጠናቀቁን የሚያበስር ሀገራዊ መድረክ ተዘጋጅቷል
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: