Search

የሀረር አባልነት ዓለም አቀፍ ጎብኚዎችን ለማሳደግ የሚረዳ ስኬት ነው - አቶ ኦርዲን በድሪ

ማክሰኞ ጥቅምት 24, 2019 51

ሀረር የአለም አቀፉ የሀር መንገድ ከተሞች የቱሪዝም ጥምረት አባል መሆኗ ከተማዋ አለም አቀፍ ትኩረት እንድትስብ የሚያግዝና ዓለም አቀፍ ጎብኚዎችን ለማሳደግ የሚረዳ መሆኑን የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ዛሬ የሀረር ከተማ በቻይና ሉዣን ከተማ የአለም አቀፉ የሀር መንገድ ከተሞች የቱሪዝም ጥምረት አባል እንደሆነች ጠቅሰዋል።

የጥምረቱ አባልነት ማረጋገጫ የሆነው መለያንም በይፋ መቀበሏን አመልክተዋል።

ከተማዋ በዚህ ታሪካዊ አባልነት ጥምረቱን መቀላቀሏ አለም አቀፍ ዕይታን እንድትስብ የሚያግዝ፣ ለአለም አቀፍ የቱሪዝም ትብብርና ኢንቨስትመንት በር የሚከፍት፣ አለምአቀፍ የዕውቀት ሽግግርና የጋራ ትውውቅን የሚያሰፋ እና አለም አቀፍ ጎብኚዎችን ወደ ታሪክ ሀብታሟ ከተማችን የሚያደርጉት ጉብኝት እንዲጨምር የሚያግዝ ነው ሲሉ ጠቁመዋል።

 

ለሀረር ከተማ ዕድነትና አለምአቀፍ  ዝና ወሳኝ መሰረት የሚጥል መሆኑንም አመልክተዋል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: