የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር የሆኑትን ቼን ሃይን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ሚኒስትሩ ከአምባሳደሩ ጋር በነበራቸው ውይይት በሁኔታዎች የማይለወጠውን የኢትዮጵያ እና የቻይና ስትራቴጂካዊ ትብብር የበለጠ አጠናክሮ መቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን፤ ሁለቱ ሀገራት በተለይም በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በአቅም ግንባታ መስኮች ያላቸውን ትብብር አጠናክረው ለመቀጠል ተስማምተዋል።
በውይይቱ ወቅት የቻይናው አምባሳደር ቼን ሃይ ሀገራቸው የመደመር መንግሥት ትልሞች ውጤታማ እንዲሆኑ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: