የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለ13 ቀናት ያካሄደውን የጥቅምት ወር ምልዓተ ጉባኤ የተለያዩ አበይት ውሳኔዎችን በማሳለፍ አጠናቅቋል።
በሀገር ሰላም፣ በቤተ ክርስቲያኗ ሁለንተናዊ ዕድገትና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በአንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠሩ ችግሮችን ለማጣራት፣ ለተጎዱት ድጋፍ ለማድረግ እና ጉዳዩን ከከፍተኛ የመንግሥት አካላት ጋር ለመወያየት ኮሚቴዎች ተዋቅረዋል።
መንፈሳዊ ኮሌጆችን በማሳደግና ስያሜ በመስጠት፣ በዓላትን በድምቀት በማክበር እንዲሁም በሀገረ ስብከቶች የታዩ የአስተዳደርና የፋይናንስ ክፍተቶችን በማረም ረገድ የተለያዩ አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ተላልፈዋል።
ቤተ ክርስቲያኗ በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ያላትን ተሳትፎ የሚያጠናክርና የሚከታተል ቋሚ ኮሚቴ ተሰይሟል።
በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶሱ ያለፉ ቅራኔዎችና አለመግባባቶች በሰላማዊ ውይይት፣ በእርቅና በይቅርታ እንዲፈቱ ሀገራዊ ጥሪ በማቅረብ ጉባኤውን በስኬት አጠናቋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: