ትናንት የተጀመረው 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች አህጉራዊ ጉባኤ "ለዕድገት መምራት" በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬም ቀጥሎ ይካሄዳል፡፡
በብልፅግና ፓርቲ አዘጋጅነት እና በአፍሪካ ገቨርናንስ ሴንተር አስተባባሪነት እየተካሄደ የሚገኘው ይህ ታላቅ መድረክ፣ የገዢና ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮችን፣ የሀገር መሪዎችን፣ ሚኒስትሮችን፣ ምሁራንና የሲቪል ማኅበራት ተወካዮችን ጨምሮ ከ1 ሺህ በላይ እንግዶች ከመላ አህጉሪቱ ተሳትፈዋል።
በአብዛኛው የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከምርጫ ውድድር አልፈው በብሔራዊ የልማት ጥቅሞች ላይ በትብብር የመሥራት ልምዳቸው አነስተኛ መሆኑና በዘውግ ፖለቲካ መጠመዳቸው ለልማት ማሽቆልቆል ምክንያት ሲሆን ቆይቷል።
ይህ የአዲስ አበባው ጉባኤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከምርጫ ፖለቲካ ባሻገር በሀገር ግንባታ፣ በኢኮኖሚ ዕድገት እና በፖሊሲ ቀጣይነት ውስጥ የለውጥ ሞተር የሚሆኑበትን አዲስ አህጉራዊ መስመር ለማስቀመጥና ለመተባበር መሠረት ይጥላል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ለቀናት በሚኖራቸው ቆይታ የሀገራቸውንና የአህጉሪቱን ዘላቂ የልማት አቅጣጫዎች በፖሊሲ መደገፍ የሚያስችሏቸው ስትራቴጂዎችን፣ ዜጎችን በተሳታፊነትና በተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ አካታች አሠራሮችን፣ በዓለም አቀፍ ተጽዕኖዎች የማይበገሩ ጠንካራ አህጉራዊ የኢኮኖሚ መዋቅሮችን መገንባት የሚያስችል ሐሳብ ይለዋወጣሉ።
በላሉ ኢታላ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: