የ2ኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ዋና ጉባኤ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በዓድዋ ድል መታሰቢያ መካሄድ ጀምሯል።
በዛሬው የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ የተለያዩ የመንግሥት ከፍተኛ ሥራ ኃላፊዎች፣ የፓርቲ ፕሬዚዳንቶችና ዋና ፀሐፊዎች፣ የፓርላማ አባላት፣ አህጉራዊ ተቋማት ኃላፊዎች እና የልማት ፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ተገኝተዋል።
ፓርቲዎች ከአህጉራዊው የነፃ ንግድ ቀጣና ጋር የተጣጣሙ የኢንዱስትሪ ፖሊሲዎችን መቅረፅ በሚችሉበት፣ የሀገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብንና ኃላፊነት የተሞላበት የብድር አስተዳደርን በማጠናከር የሕዝብ እምነት በሚገነቡበት እንዲሁም ከግሉ ዘርፍ ጋር ዘላቂ አጋርነት በሚፈጥሩበት ጉዳይ ላይ በስፋት ይመክራሉ።
በተጨማሪም የፖለቲካ አመራሮች ከአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት ጋር የተጣጣመ የረጅም ጊዜ የልማት ራዕይ በመቅረፅ፣ ለአህጉሪቱ ዘላቂ የኢኮኖሚ ጉዞ የጋራ አቋም ይይዛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በሐና ምንዳሁን
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: