Search

ተኪ ምርቶች በማምረት ላይ የቴክኒክ እና ሙያ ሰልጣኞች ሚና

ሰኞ ነሐሴ 19, 2017 42

 

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከፌደራል ቴክኒክ እና ሙያ ኢኒስትቱዩት ጋር በመቀናጀት በኢትዮ ስኪልስ ሰመር ካምፕ ፕሮግራም የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ አየሰሩ ይገኛሉ። 

በኢትዮ ስኪልስ ሰመር ካምፕ ያሉ ሰልጣኞች በተቋሙ ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ እና የፈጠራ ብቃታቸውን ተጠቅመው ወደ ሥራ እንዲገቡ የላቀ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል 

በሰመር ካምፑ ተኪ የሀገር ውስጥ ምርትን ለማበረታታት በተለይም የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለማዳበር፤ ለሰልጣኞች ድጋፍ እየተደረገላቸው ሲሆን በዚህም አመርቂ ውጤት እየታየ እንደሆነም የተነሳው

ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ወደ ሀገር ውስጥ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት የውጭ ምንዛሬን ማዳን መቻሉም ተጠቁሟል

በኢትዮ ስኪልስ ሰመር ካምፕ የሰሚ አውቶሜድ ቻርኮል የእንስሳት መኖ ማምረቻ ማሽን፣ የማንዋል ፕላስቲክ ኢንጀክሽን ሞዴሊንግ ማሽን፣ ለአርሶ አደሮች እረፍት የሚሰጥ ፋርሚንግ ቴክኖሎጂ ማሽን እና ሌሎችም ተኪ ምርቶች ተመርተዋል።

በኢትዮጵያ ታምርት እና የኢትዮጵያን ይግዙ ንቅናቄን ለማበረታታት፤  የቴክኒክ እና ሙያ የቴክኖሎጂ ማሰልጠኛ ተቋሞች ችግር ፈቺ ተኪ ምርቶችን በመፍጠር እና በማምረት ጉልህ አስተዋፅኦ እንዳላቸውም ተገልጿል

በሔለን ተስፋዬ