Search

አገልግሎትን በቤት ለማግኘት የሚያስችለው የዲጂታል ዓለም

ሰኞ ነሐሴ 19, 2017 37

ሰዎች ወደ ዲጂታሉ ዓለም በገቡ ቁጥር አንዳንድ አገልግሎቶችን በቤታቸው ሆነው እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን የፋይዳ ዲጂታል ብሔራዊ መታወቂያ ከፍተኛ አማካሪ ኦላና አበበ ገልፀዋል።

እንደ ንግድ ፍቃድ እና መንጃ ፍቃድ እድሳት ያሉ አገልግሎቶችን ከቤት ሆኖ ማግኘት እንደሚቻል ጠቅሰዋል።

ወደ ዲጂታሉ ዓለም ለመግባት ደግሞ አንዱ መንገድ ዲጂታል መታወቂያ መሆኑን ነው አማካሪው ያነሱት።

ዲጂታል መታወቂያ የሰዎችን ማንነት ከማሳወቅ ባሻገር ተቋማትን የሚያስተሳስር፣  አገልግሎቶችን የሚያፋጥን እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚያስቀር ነው ብለዋል።

በእድሜ፣  በአደጋ ወይም በአካል ጉዳት ምክንያት አሻራቸው ያልተነበበ ዜጎችም ምዝገባ ማድረግ እንደሚችሉ እና በልዩ ሁኔታ እንደሚመዘገቡ አንስተዋል።

በ2018 ዓ.ም ለ40 ሚሊዮን ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ለማድረግ እቅድ መያዙንም ነው አማካሪው የጠቁሙት።

በሴራን ታደሰ

#Digital_Ethiopia #Digitalworld #DigitalID