Search

በሌሎች ሀገራት የቴክኖሎጂ ገበያ ለመሳተፍ እየተሠራ ነው - የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ

ማክሰኞ ነሐሴ 20, 2017 96

ኢትዮ ቴሌኮም የገበያ አድማሱን በማስፋት በሌሎች ሀገራት የቴክኖሎጂ ገበያ ለመሳተፍም እየተሠራ ነው ሲሉ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ተናገሩ።

ኢትዮ ቴሌኮም “ቀጣይ አድማስ /NEXT HORIZON /” የተሰኘ የቀጣይ 3 ዓመታት ስትራቴጂውን በሳይንስ ሙዚየም ይፋ አድርጓል።

በወቅት ፍሬሕይወት ታምሩ ፤ ኢትዮ ቴሌኮም በዲጂታል ቴክኖሎጂ በዓለም ብቁ እንዲትሆን እየሠራ ነው ብለዋል።

የሀገሪቱ ሁለንተናዊ የልማት ዕቅዶችንና ፖሊሲዎች ባማከለ መልክ ስትራቴጂው እንደሚተገበርም ገልፀዋል።

ስትራቴጂው አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ በማድረግ ሰው ተኮር በሆነ መልኩ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በአዲሱ ስትራቴጂ ስድስት ትኩረት ጉዳዮች መኖራቸውን ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ አስረድተዋል።

ዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ፣ የፋይናንስ ቀጣይነት እና ጥንካሬ ፣ ብቁ እና ንቁ አሰራሮች እና በኃላፊነት ስሜት በታዓማኝነት ማገልገል ዋናኛ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውንም አንስተዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ቀጣይ የሶስት ዓመት ስትራቴጂ "ቀጣይ አድማስ " ይፋ ማድረጊያ ስነ ስርዓት


በትዕግስቱ ቡቼ


#EBC #ebcdostream #digital #Ethiopia