Search

በሰዓት 70 ማይል የሚጓዝ የአቧራ አውሎ ንፋስ በአሜሪካ ተከሰተ

ማክሰኞ ነሐሴ 20, 2017 289

ነዋሪዎችን ለአደጋ ያጋለጠ ከባድ የአቧራ አውሎ ነፋስ በአሜሪካ አሪዞና በምትገኘውን ፊኒክስ ከተማ ተከስቷል።

በሰዓት 70 ማይል የሚጓዘው የአቧራ አውሎ ንፋሱ ከ60 ሺ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች የኃይል አቅርቦት መቋረጥ ምክንያት ሆኗል።

"ሀቦብ" በመባል የሚጠራው አውሎ ነፋሱ የፊኒክስ ስካይ ሃርበር ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በረራዎችን ለአንድ ሰዓት ያክል እንዲዘገዩም አስገድዷል።

ከዚህ ባሻገር ከፊኒክስ በስተደቡብ ምስራቅ 22 ማይል ርቀት ላይ ወደምትገኘው ጊልበርት በሚወስደው መንገድ ላይ ዛፎች በመውደቃቸው እና የትራፊክ መብራት በመቋረጡ ፖሊስ ነዋሪዎች ከመንገድ እንዲርቁ አሳስቧል።

በአሪዞና የዝናብ ወቅት የአቧራ አውሎ ነፋሶች የተለመዱ ቢሆኑም የአሁኑ ከወትሮው በተለየ ኃይለኛ መሆኑን ሴኤንኤን ዘግቧል።



በሴራን ታደሰ