Search

በመስኖ ልማት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ

ሓሙስ ታኅሣሥ 09, 2018 35

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በመስኖ ልማት ስራዎች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በስፋት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዱብቲ ወረዳ በከፊል አርሶ አደሮች እየለሙ የሚገኙ የግብርና ስራዎች ላይ ምልከታ አድርገዋል። 

በዱብቲ ወረዳ በከፊል በ126 ሄክታር እየለማ ከሚገኘው የሽንኩት እርሻ ከፍተኛ ምርት እየተሰባሰበ እንደሚገኝ ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል።

በወረዳው የሚገኘው  የመስኖ ልማት አማራጭ እና ያለውን ለም መሬት በአግባቡ በመጠቀም ህብረተሰቡ ከተረጂነት እንዲላቀቅ እየተሰራ ባለው ስራ ለውጥ ስለመገኘቱ ርዕሰ መስተዳድሩ አንስተዋል።

በክልሉ ከለውጡ በፊት የብዙ ግዜ ጥያቄ የነበረውን የማዳበሪያ ጥያቄ ምላሽ በመስጠት በሁሉም ወረዳዎች አትክልት እና ፍራፍሬ እንዲሁም በሰብል ምርት ትልቅ እመርታዎች እየተመዘገቡ ይገኛሉ ሲሉ ገልፀዋል።

በዘንድሮ ዓመት ካለፈው አመት የተሻለ ምርት ለመሰብሰብ በስፋት እየተሰራ እንደሚገኘ ርዕሰ መስተዳድሩ አንስተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ የጎበኙት በዱብቲ ወረዳ ጉርሙዳሌ እና ዲዳሌይታ ቀበሌ በህብረተሰቡ ብቻ እየለማ የሚገኘ የግብርና ስራዎችን ነው።

በሁሴን መሀመድ