የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለሚታዘቡና መሥፈርቱን ላሟሉ 45 የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች የዕውቅና ሰርተፍኬት መስጠቱን አስታውቋል።
ቦርዱ ቀደም ሲል የታዛቢዎችን የምዝገባ ሂደት ቀልጣፋ፤ የመረጃ አደረጃጀቱንም ዘመናዊ ለማድረግ ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለሚታዘቡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መስጠቱ ይታወሳል።
#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #election #observers