Search

የኢትዮጵያ የከፍታ ጎዞ

ረቡዕ ታኅሣሥ 08, 2018 84

ከዓለም ቀድማ የነቃች የስልጣኔ ምድር የነበረችው ኢትዮጵያ በዘመናት ሂደት ወደ ኋላ ቀርታ ኖራለች።

አሁን ላይ ደግሞ አቅሞቿን ተጠቅማ ወደ ፊት ለመስፈንጠር ጉዞ ጀምራለች።

ችግሮቿን አራግፋ ለመጣል በቁጭት የተነሳችው ኢትዮጵያ፣ በእርግጥም የተስፋ ሀገር ሆናለች።

ባለፉት ዓመታት የመደመር መንግሥት የጀመራቸው ውጥኖች ፍሬ እያሳዩ መጥተዋል። ይህ ውጤት ሁለንተናዊ እንደሆነም ይገለፃል።

የኢትዮጵያ ማንሰራራት ከተረጂነት የመላቀቅ፣ ራስን የመቻል እና ወደ ብልጽግና ለመስፈንጠር የመነሳት ጭምር ነው።

ለዚህም የችግሮቹን መንስዔ ከመፈለግ በመጀመር ለውጤቱ ደግሞ በትጋት መሥራት ያሻል።

አሁን ላይ በኢትዮጵያ ትልቅ የይቻላል አብዮት ተቀጣጥሏል፤ በዚህ ወኔዋ በአፍሪካ ቀዳሚ ስንዴ አምራች ሀገር ለመሆን በቅታለች፤ እንደ ሩዝ ያሉ ሌሎች ምርቶች ላይም ከፍተኛ እመርታ ተመዝግቧል።

ለውጡ በግብርና ዘርፍ ብቻ የታጠረ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ማንሰራራት የማዕዘን ድንጋይ የሚሆኑ ትላልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችንም እውን እያደረገ ያለ ነው።

ግንባታው የተጠናቀቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን አንዱ ማሳያ ነው።

30 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ተጨማሪ ግዙፍ ፕሮጀክቶችም በቅርቡ ተጀምረዋል።

ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ሁሉንም የኢትዮጵያ አቅሞች ወደ ልማት በመቀየር ስኬት አስመዝግቧል።

በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በግብርና፣ በቱሪዝም፣ በአይሲቲ እና መሰል ዘርፎችም ከፍተኛ ለውጥ ታይቷል።

በኢትዮጵያ ምድር ምርት እና ምርታማነትም በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ ነው።

የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዘመዴነህ ንጋቱ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ ትልቁ የአውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት እንዲሁም ሰባቱ የ30 ቢሊዮን ዶላር የጉባ ብስራቶች የወደፊቱ ኢትዮጵያ የዕድገት ማሳያ ስለመሆናቸው ተናግረዋል።

በተለይም ባለፈው ታሪካችን ያጣናቸው ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን መልሶ ለማግኘት መሥራት ብልህነት ነው ያሉት አቶ ዘመዴነህ፤ ትልቅ ለውጥ የሚፈጥሩ ዘርፎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ስላለው ፋይዳ አፅንዖት ሰጥተው ገልጸዋል።

በሜሮን ንብረት

#ebcdotstream #EBC #Ethiopia