Search

የመጀመሪያው የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት ጉባዔ በኢትዮጵያ ይካሄዳል

ማክሰኞ ኅዳር 23, 2018 153

የአፍሪካ ህብረት ያዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የኢነርጂ ውጤታማነት ጉባዔ (Energy Efficiency Conference) ታህሳስ 2 እና 3 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው የህብረቱ ዋና መቀመጫ ይካሄዳል።

ጉባዔው እ.አ.አ በ2024 በአዘርባጃን ባኩ በተካሄደው 29ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (ኮፕ 29) ይፋ በተደረገው የአፍሪካ ኢነርጂ ውጤታማነት ጥምረት ማዕቀፍ ሥር የሚካሄድ ነው። የጥምረቱ ማዕቀፍ በአፍሪካ ህብረት ሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መጽደቁ ይታወቃል።

“የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳን በስትራቴጂያዊ አጋርነት እውን ማድረግ” የጉባዔው መሪ ሀሳብ ነው።

አህጉራዊው ሁነት የተዘጋጀው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተቋም በሆነው የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን እና በኢትዮጵያ መንግሥት ትብብር ነው።

ጉባዔው የኢነርጂ ውጤታማነትን በማረጋገጥ የአፍሪካ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የዘላቂ ልማትና የአየር ንብረት ለውጥ ተግባራዊ ምላሽ አቀጣጣይ ሞተር የማድረግ ዓላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል።

ከአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት ኮንፍረንስ ጎን ለጎን ሌሎች ተጓዳኝ ሁነቶች እንደሚከናወኑም ታውቋል።

#EBC #ebcdotstream #Africa #AU #Energy #AFREC #Ethiopia