በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከጅቡቲ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ ጋር ውይይት አድርጓል።
የልዑካን ቡድኑ ከፕሬዝዳንቱ ጋር በነበረው ቆይታ በቀጠናው ተምሳሌታዊ የሆነውን የሁለቱን ሀገራት ትስስር ይበልጥ በማጠናከር ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክሯል።
በተጨማሪም ሁለቱ ሀገራት በጋራ የሚያስተዳድሯቸው ፕሮጀክቶች አፈጻጸምን ገምግሟል።
የልዑካን ቡድኑ በተጨማሪም የዶራሌ ሁለገብ ወደብን የጎበኘ ሲሆን፣ ወደቡ ለኢትዮጵያ ወጪ እና ገቢ ምርቶች እየሰጠ ያለውን አገልግሎት እንዲሁም ከወደቡ በባቡር ከባድ ጭነትን ወደ ሀገር ቤት የማጓጓዝ እንቅስቃሴ ያለበትን ሁኔታ ተመልክቷል።
የልዑካን ቡድኑ ተልዕኮውን አጠናቆ ማምሻውን ወደ ሀገር ቤት መመለሱን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመልክቷል።
#Ebc #Ebcdotstream #Ethiopia #Djibouti