Search

የግል አቪዬሽን ድርጅቶች እራሳቸውን ብቁና ተወዳዳሪ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል - የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን

ማክሰኞ ነሐሴ 20, 2017 201

የግሉ አቪዬሽን ድርጅቶች እራሳቸውን ብቁና ተወዳዳሪ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ሲል የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ገልጿል።
ባለስልጣኑ ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ጋር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ የግል ተቋማት ተሳትፈዋል።
በወቅቱ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ አበራ፤ ተቋማቸው ለመንግሥትም ሆነ ለግሉ የአየር ትራንስፖርት አቅራቢዎች እኩል አሰራር እንዳለው ተናግረዋል።
በአየር ትራንስፖርቱ ሰፊ ፍላጎት በመኖሩ የግል አየር ትራንስፖርት ሰጪዎች በአገልግሎቱ ተመራጭ ለመሆን ይበልጥ መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
የግል አቪዬሽን ድርጅቶቹ በቀጣይ ራሳቸውን ለዓለም አቀፍ በረራዎች ዝግጁ ከማድረግ ጀምሮ በርካታ ሥራዎችን መስራት እንዳለባቸው ተመላክቷል።
በመለስተኛ የአየር ማረፊያዎች ላይ የሚታየውን የመሰረተ ልማት ውስንነት ለመፍታት የግሉ ዘርፍ ከመንግሥት ጋር በጋራ በማልማት አጋርነቱን ሊያሳይ እንደሚገባ ተገልጿል።
 
 
በሃብተሚካኤል ክፍሉ