Search

ወደ ልማት ብርሃን የተሻገረው

ዓርብ የካቲት 27, 2018 72

ተፈጥሮ በልግስና ያደላችለት ቄለም ወለጋ፣ ዛሬ የልማት ጥማቱን በሥራና በጥረት እያካካሰ ይገኛል።
በአካባቢው የነበረው የሰላም መደፍረስ የሕዝቡን የልማት መሻት ቢያዘገየውም፣ በመንግሥት ቁርጠኝነትና በማኅበረሰቡ ንቁ ተሳትፎ ያ ተግዳሮት ታሪክ ሆኗል። ዛሬ አካባቢው ከጸጥታ ስጋት ወጥቶ ትኩረቱን ሙሉ በሙሉ ወደ ልማት አዙሯል።
ቀደም ሲል ምርታማ መሆን አለመቻላቸውን በቁጭት የሚያስታውሱት የአካባቢው አርሶ አደሮች፣ አሁን ግን ሰላምን ተንተርሰው በመስኖ ስንዴ ልማት ላይ ስኬትን እያጨዱ መሆኑን ተናግረዋል።
የግብርና ባለሙያዎች የሚሰጧቸው ሥልጠናም የልምድ እውቀታቸውን በማዘመን፣ ከራሳቸው አልፈው ለሀገር ብልጽግና ትልቅ ድርሻ እንዲያበረክቱ አቅም ሆኗቸዋል።
በቄለም ወለጋ ዞን የጊዳሚ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት ዋቅጋሪ ደበላ እንደገለጹት፣ቀደም ሲል የሰላም እጦት በነበረባቸው 28 የገጠር ቀበሌዎች ዛሬ ከ16 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ስንዴ እየለማ ይገኛል።
በዞን ደረጃም በ150 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከ5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ግብ ተቀምጦ በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው። ይህ ስኬት የቄለም ወለጋን ሰላም በማስጠበቅና የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለውን ጥረት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
በአፎሚያ ክበበው