Search

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የእጩዎች ዝርዝር ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ይፋ ይደረጋል - ምርጫ ቦርድ

ዓርብ የካቲት 27, 2018 63

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደሩ እጩዎች ዝርዝር ከዛሬ ምሽት ጀምሮ በየምርጫ ክልሎቹ ይፋ እንደሚደረግ አስታውቋል።

የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ እንደገለጹት፤ ቦርዱ በፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረቡለትን የእጩዎች ዝርዝርና ተያያዥ ሰነዶችን በጥንቃቄ የመመርመር ሥራውን አጠናቋል።

በዚህ የምርጫ ሒደት 47 ፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሳተፉ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 10 ሺህ 934 እጩዎች ለምርጫ ቀርበዋል።

ከእነዚህም መካከል 2 ሺህ 198 እጩዎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ 8 ሺህ 736 እጩዎች ደግሞ ለክልል ምክር ቤቶች የሚወዳደሩ ናቸው።

በምዝገባው ሂደት 73 የግል እጩዎች የተካተቱ ሲሆን፣ ከጠቅላላው የእጩዎች ቁጥር ውስጥ 2 ሺህ 760 ሴቶችና 8 ሺህ 174 ወንዶች መሆናቸውን ቦርዱ ገልጿል።

በምርጫው ለመሳተፍ ከተመዘገቡ 47 ፓርቲዎች ውስጥ ስምንት እና አራት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያካተቱ ሁለት ጥምረቶች እና አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች የተካተቱበት አንድ ግንባር እንደሚገኝበት ተመላክቷል።

በሳምሶን ገድሉ

#EBC #Ethiopia #Election2018 #NEBE #Democracy #Candidates #ኢትዮጵያ #ምርጫ2018