Search

የምርጫ ዓይነቶች እና አፈጻጸማቸው በኢትዮጵያ

ቅዳሜ የካቲት 28, 2018 46

በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 (ከአንቀጽ 6 እስከ 11) መሠረት የምርጫ ዓይነቶች እና አፈጻጸማቸው እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፦

ጠቅላላ ምርጫ

የሕዝብ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ ሲሆን፣ በየአምስት ዓመቱ በመላው ኢትዮጵያ በተመሳሳይ ጊዜ ይካሄዳል።

የአካባቢ ምርጫ

ከብሔረሰብ ዞን እስከ ቀበሌ ያሉ የምክር ቤት አባላት ምርጫ ነው። ዝርዝር አፈጻጸሙ ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል።

ማሟያ ምርጫ

የተጓደሉ መቀመጫዎችን ለመሙላት ወይም የ"ይውረድልን" ጥያቄ ሲቀርብ የሚደረግ ነው። ቦርዱ ጥያቄው በደረሰው በ6 ወራት ውስጥ ማከናወን አለበት። ሆኖም የምክር ቤቱ የሥራ ዘመን ሊያበቃ 6 ወር እና ከዚያ በታች ከቀረው ምርጫው አይካሄድም።

ድጋሚ ምርጫ

የምርጫ ውጤት ሲሰረዝ ወይም እጩዎች እኩል ድምፅ ሲያገኙ የሚከናወን ነው። አዲስ ምዝገባ ሳያስፈልግ በቀድሞ መራጮች ብቻ ይካሄዳል።

ሕዝበ ውሳኔ (Referendum)

የሕዝብን ፍላጎት ወይም ውሳኔ ለማወቅ የሚደረግ የድምፅ አሰጣጥ ሥርዓት ነው።

ኢትዮጵያ ዘንድሮ የምታካሂደው ጠቅላላ ምርጫ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሂደቱ አስፈላጊውን ዝግጅት እያጠናቀቀ ይገኛል። የመራጮች ምዝገባም ዛሬ ተጀምሯል።

በለሚ ታደሰ

#EthiopiaElections #Proclamation1162 #NEBE #ElectionLaw #GeneralElection #Referendum