ነገ ቅዳሜ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ የሚከናወነውን ታላቁን የኢፍጣር መርኃ ግብር ምክንያት በማድረግ፣ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚካሄደውን ይህንን መርሐ-ግብር ተከትሎ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የሚከተሉት መንገዶች ዝግ ይደረጋሉ፦
በተጠቀሱት መንገዶች ላይ ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት አቁሞ መሄድ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ አሳስቧል።
ኅብረተሰቡ ለፀጥታ ሥጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በነጻ የጥሪ መስመሮች 990፣ 991፣ 987፣ 816 እንዲሁም በ011-1-26-43-59፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 በመደወል ወይም በEFPApp መተግበሪያ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።